Telegram Group & Telegram Channel
"በዓለ ኤጲፋንያ እስመ በይእቲ ዕለት አስተርአየት መለኮቱ ለክርስቶስ ፣ ኤጲፋንያ ዝ ውእቱ ሕፅበት ዘቦቱ አስተርአየ እግዚእ ወመድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኵሉ ሰብእ በፈለገ ዮርዳኖስ በብርሃነ መለኮቱ ⇨ የኤጲፋንያ በዓል በዚህች ዕለት የክርስቶስ መለኮቱ የታየ(ች)በት። ኤጲፋንያ መታጠብ ነው፤ በኤጲፋንያ ጌታ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ሁሉ በመለኮታዊ ብርሃኑ ለሰው ሁሉ በዮርዳኖስ ወንዝ የተገለጠበት ነው። 【ሲኖዶስም ትዕዛዝ ፷፮ 】

የሥርዓተ ጽዮን መጽሐፈ ቀኖና ፴ ከሚሆነው የቀኖና ክፍል በስፋት የተብራራው ስለ በዓለ ሰንበት አከባበር፣ ስለ ጾመ ጋድ (ገሐድ) እና ስለ ኤጲፋንያ በዓለ አስተርእዮ ነው።

ሠለስቱ ምዕትም በሃይማኖተ አበው ስለጾም በደነገጉት አዋጅ አጲፋንያ ጥምቀት መሆኑን አመልክተዋል።
" ወኢትትዐደው ጾመ ዘእግዚአብሔር ዘውእቶሙ ረቡዕ ወዐርብ ዘእንበለ ይርከብከ ደዌ ክቡድ ወዘእንበለ መዋዕለ ጰንጠቆስጤ ወበዐለ ልደት ወበመዋዕለ አስተርእዮ ዘውእቱ ኤጲፋንያ ➨ ጌታ ያዘዘውን ጾም አትሻር እነዚህም ረቡዕ ዓርብ ናቸው ደዌ ካላገኘህ በቀር በበዓለ ሐምሳ፣ ልደት ፣ ጥምቀት በዋሉባቸው ዕለታት (ረቡዕ ዐርብ) በቀር ይኸውም ኤጲፋንያ (ጥምቀት) ነው።" 【ሃይ. አበው ዘ፫፻ ፳፥፲፰】

በሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዘመነ አስተርእዮ (Epiphany season) ዴናህ/ዴንሃ【 ܕܢܚܐ 】እየተባለ ይጠራል። በጊዜ ሰሌዳ ከጌታችን ልደት በኋላ እስከ ዐቢይ ጾም ድረስ ጾመ ነነዌንም ጭምር ይዞ ይቆያል። በዚህ ወቅት ያሉ ስምንቱን ዕለተ ዐርብ ደግሞ መታሰቢያ በመስጠት በተለየ መንገድ ያከብሩታል። የመጀመሪያው ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት ፣ ሁለተኛውን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ፣ ሦስተኛውን ዓርብ ለወንጌላውያን ፣ ቀጣዩን ደግሞ ለቅዱስ እጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት እያሉ የመጨረሻውን ለቤተክርስቲያን ጠባቂዎች/ ገበዝ (The Patron of the Church) ሰጥተው ያከብራሉ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም ሥርዓትና ደንብ በዚህ ወቅት በዓለ ዲያቆናት (✤ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጥር ፩) በዓለ ሐዋርያት (✤ ቅዱስ ዮሐንስ ጥር ፬) እንዲሁም በዓለ እግዝእትነ ማርያም (✤ አስተርእዮ ማርያም ጥር ፳፩) በልዩ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል።

( ክፍል ፪ ይቀጥላል… )

✍️ በዓለ ጥምቀት ፳፻፲፭ ዓ.ም. የተፃፈ

tg-me.com/orthodox1/13086
Create:
Last Update:

BY ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283

Share with your friend now:
tg-me.com/orthodox1/13086

View MORE
Open in Telegram

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Dump Scam in Leaked Telegram Chat

A leaked Telegram discussion by 50 so-called crypto influencers has exposed the extraordinary steps they take in order to profit on the back off unsuspecting defi investors. According to a leaked screenshot of the chat, an elaborate plan to defraud defi investors using the worthless “$Few” tokens had been hatched. $Few tokens would be airdropped to some of the influencers who in turn promoted these to unsuspecting followers on Twitter.

For some time, Mr. Durov and a few dozen staffers had no fixed headquarters, but rather traveled the world, setting up shop in one city after another, he told the Journal in 2016. The company now has its operational base in Dubai, though it says it doesn’t keep servers there.Mr. Durov maintains a yearslong friendship from his VK days with actor and tech investor Jared Leto, with whom he shares an ascetic lifestyle that eschews meat and alcohol.

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 from us

Telegram ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
FROM USA